Lina Getachew

ሊና ጌታቸው እባላለሁለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለአዲሱ ዘመን በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ! በተጨማሪ ለመላው ህዝበ ክርስትያን መልካም የመስቀል በዓል እመኛለሁ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ነው ተወልጄ ያደግኩት። 18 አመት እድሜዬ በታወቀውና በአሜሪካ በሚገኘው ዬል ዩኒቨርሲቲ/Yale University/የትምህርት ዕድል ተሰጥቶኝ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪዬን (የማስተርስ ዲግሪዬን) ለማግኘት በቅቻለሁ። ለቋንቋዎችና አለምን ለማየት ባለኝ ፍላጎት ምክንያት የዬል ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለሁ የፈረንሳይኛ እና የስፓኒሽ ቋንቋዎችን በጥልቅ ሁኔታ ተምሬያለሁ።በፈረንሳይ ሀገር በፓሪስ ከተማም ቆይታ በማድረግ የፈረንሳይኛ ችሎታዬን ለማዳበር ችያለሁ። ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ ከሌሎችየዬል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ተወዳድሬ በማሸነፍ ቻንግሻ የሚባል የቻይና ከተማ ውስጥ በሚገኝ የታወቀ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ(Xiangya Medical School 湘雅医学院) ሌክቸረር ሆኜ በማገልገሌ ትምህርትን እንዴት በቀላሉ ወደ ተማሪዎች ማስተላለፍእንደሚቻል ለመገንዘብም በቅቻለሁ። በቻይና ሀገር መኖር ከጀመርኩ በኋላ ነው ቻይንኛ መማር የጀመርኩት። ከሌላ ሀገር ከመጡዜጎች ይልቅ ትምህርቱ በቀላሉ ይገባኝ ነበር። ይህም የሆነው ቻይንኛ ለአማርኛ ተናጋሪዎች ስለሚቀል ነው። ቻይና እና ኢትዮጵያግንኙነታቸው እየጠነከረ በመምጣቱ ኢትዮጵያውያን በቀላሉ ቻይንኛ መማር እንዲችሉ ብዬ ነው ይህንን መፅሐፍ ለመፃፍ የወሰንኩት።በአሁኑ ሰዓት በቻይና እና በአፍሪካ ማህል ያለውን ግንኙነት እያጠናሁ ሲሆን ጥናቶቼም በተለያዩ የጥናትና ምርምር ተቋሞችታትመዋል። በዚህ አጋጣሚ እናቴ / ፀዳሉ በላይ እና አባቴ አቶ ጌታቸው አየነው በትምህርቴ እንድገፋ ላደረጉልኝ ገደብ የሌለውድጋፍ እጅግ እጅግ በጣም አመሰግናቸዋለሁ።

1.        ቋንቋ ለሰው ልጅ ያለውን ጥቅም እንዴት ትገልጭዋለሽ?

ቋንቋ መግባቢያ ብቻ ሳይሆን የማንንነት መገለጫና ዝምድና መፍጠር የሚያስችል መሳሪያ ነው። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ውብ የሆኑ ቋንቋዎች ይገኛሉ። እነዚህ ቋንቋዎች የተናጋሪዎቹን ባህል ከማጠንከርም በላይ ማንነታቸውን ይገልፃሉ። እንደገናም ደግሞ አንድ ሰው ከአፍ መፍቻ ቋንቋው ውጪ ሌላ ቋንቋ ቢማር ከሌሎች ህዝቦች ጋራ ጥሩ የሆነ ግንኙነት የመፍጠር እድል ያገኛል። ለምሳሌ እኛ ሀገር ውስጥ አማርኛ የሚናገር ፈረንጅ ሲያጋጥመን ከሌሎቹ ፈረንጆች ሁሉ ለይተን እናቀርበዋለን። ይህም የሆነበት ምክንያት በቋንቋችን ሰለተዛመደን ነው።

2.       ከሌሎች ርዕሶች በተሻለ ቋንቋ ላይ ለምን መስራት ፈለክሽ?

ከልጅነቴ ጀምሮ በእርግጥ የቋንቋ ፍቅር ነበረኝ። ነገር ግን አሁን የቻይና ኢኮኖሚ ሀይል እየተስፋፋ በመሄዱ እና እኔ ደግሞ እድሉ አጋጥሞኝ ቻይንኛ ስለተማርኩ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ብዬ ነበር እዚህ ስራ ውስጥ የገባሁት።

3.       አሁን አሁን የኛ አገር ወጣት እንግሊዘኛ መናገር ፋሽን ያደረገበትና የአዋቂነት መለኪያ እያደረገው ይገኛል! በዚህ ላይ ምን አይነት አስተያየት አለሽ?

እውነት ለመናገር ይህ ጥሩ ያልሆነ አስተሳሰብ እኔም ልጅ እያለሁ ያጠቃኝ ነበረ። እንግሊዘኛ የዘመናዊነት መገለጫ ይመስለኝ ነበረ። ነገር ግን አሜሪካ ውስጥ ሆኜ ከሌሎች የእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች ጋራ ስገናኝ የሀገሬን ቋንቋ በጣም ማክበር ጀመርኩ። የውጭ ሀገር ዜጎችም የሚያከብሩን የራሳችንን ስናውቅና ስናከብር ነው።

የዘመኑ ወጣቶች ላይ መፍረድ አይቻልም። የሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለምሳሌ በእንግሊዘኛ ስራቸውን ስለሚያከናውኑ እንግሊዘኛ ማወቅ ከቀለም ትምህርት ጋራ እንዲቆራኝ አድርጎታል። ስለዚህ የእንግሊዘኛ ቋንቋ በሀገራችን ትልቅ ሚና ይጫወታል። ተማሪዎች ይህ ቋንቋ እንደትልቅ ነገር ሆኖ ቢታያቸው ሊገርመን አይገባም።

Read more: Lina Getachew

ይከተሉን!