እሺ ለ አድዋ

እሺ ለአድዋ የአንድ መቶ ሀያኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ኪነጥበባዊ ትእይንት በስኬት ተጠናቀቀ። የራፋቶኤል የማስታወቂያና ምዕላድ ድርጅት ‪#‎ማእደ_አድዋ‬ ‪#‎የፀሐይቱ_ምሽት‬ እና ‪#‎እሺለአድዋ‬ በተሰኙ ሶስት መርሃግብሮች አንድ መቶ ሀያኛውን የአድዋ ድል ዘክሮ አልፏል። ያለፈው እሮብ የካቲት 23/2008ዓ.ም 120ኛውን የአድዋ ድል በአል አስመልክቶ በኤልያና ሆቴል በድምቀት አክብራል፡፡

 

  

“እሺ ለአድዋ”

          እሺ ለአድዋ አንድ መቶ ሀያኛውን የአድዋ ድል በተለያዩ መርሃ ግብሮች ለማክበር በራፋቶኤል የማስታወቂያና ምዕላድ ድርጅት የተሰናዳ የስራ አቅድ ነው፡፡ ይህ የስራ እቅድ የካቲት 23 ቀን 2008 ዓ/ም በኤሊያና ሆቴል ውስጥ ለማቅረብ የታቀደ ኪነጥበባዊ ትእይንት ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ የሚከተሉት ትእይንቶች ለእይታ ይቀርባሉ፡

1.    ጥንታዊ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ነገስታት አልባሳትን የሚያስቃኝና በይዘቱ በከተማችን የመጀመርያ የሆነ የፋሽን ትርኢት
2.    ታዋቂ ስድስት ባለሙያዎችን የሚያሳትፍ የስእልና የፎቶ ኤግዚብሽን
3.    ታሪካዊ ቲያትር

አድዋ
            ለመላው የጥቁር ህዝብ የስልጣኔን ጮራ የፈነጠቀችው አገራችን ኢትዮጵያ በቁርጥ ቀን ልጆቿ ዳግም ለመላው የጥቁር ህዝብ የነፃነት ጮራን አድዋ ላይ መፈንጠቅ ችላለች፡፡ ቅኝ ገዝዎች ብዙሃኑን አፍሪካውያንን ወንድሞቻችንን በባርነት ቀንበር ስር አድርገው አሀጉራችን አምቃ የያዘቻቸውን ሃብቶች ይቀራመቱበት የነበረው ያ  የእስራት ቀንበር መሰባበር የጀመረው በጀግና አያቶቻችንን በአድዋ ላይ የተፈጠረው “ ይቻላል” የሚለው አእምሯዊ መነቃቃት በመላው የጥቁር ህዝብ ላይ ሲሰርፅ ነበር፡፡
          እኛ የአያቶቻችን ልጆች ዛሬ ላይ ቆመን ትናንትን አሻግረን እየተመለከትን አንድ መቶ ሀያኛውን የአድዋ ድል ‘እሺ ለአድዋ” ብለን በሰየምነው ኪነጥበባዊ ትእይንት መዘከራችንም ወጣቱ ትውልድ በተሰማራበት የትምህርት እና የስራ ዘርፍ ላይ ውጤታማ መሆን የሚያስችለውን  “ይቻላል” የሚለውን አእምሯዊ መነቃቃት በስፋት እንደያጎለብት ለማንቃት ነው፡፡

 

ይከተሉን!