Events

                    እሺ ለ አድዋ !

ራፋቶኤል የማስታወቂያና ምዕላድ ድርጅት ከ ዳንቲና ኢኒሼቲቭ፣ ከናሁ ቲቪ እንዲሁም ከባለ አራት ኮከቡ ኤሊያና ሆቴል ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን የ120ኛውን የአድዋ ድል በአል የፊታችን እሮብ የካቲት 23 ቀን በኤሊያና ሆቴል መርቆ ይከፍታል፡፡ በእለቱም የተለያዩ ኪነጥበባዊ ትዕይንቶች የሚቀርቡ ሲሆን የተለያዩ ከፍተኛ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች እንዲሁም አባት አርበኞች በዝግጅቱ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡

                               

 

ማዕደአድዋ

በራፋቶኤል የማስታወቂያና ምዕላድ ድርጅት እና በአዲስ ጉርሻ ሬስቶራንት ትብብር የተሰናዳው “ማዕደ አድዋ” ፕሮግራም እሁድ ግንቦት 3 ቀን 2007 ዓ/ም በአዲስ ጉርሻ ሬስቶራንት ተደርጓል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር የስራ አመራሮችና አባቶች እንዲሁም ሰአሊ ብሩክ የሺጥላ በክብር እንግድነት ታድመው ንግግሮችን አድርገዋል፡፡ በተጨማሪ የስእል እና የፎቶ ኤግዚብሽን የሽለላ ትርኢትና የእራት ግብዣ የፕሮግራሙ ግብአቶች ነበሩ፡፡

የፕሮግራሙ አዘጋጆች እንደገለፁልን “ማዕደ አድዋ” በመጪው አመት የሚከበረውን አንድ መቶ ሀያኛውን የአድዋ ድል በአል ከሰኔ 2007 አንስቶ ለዘጠኝ ተከታታይ ወራት ለማክበር የተዘጋጀ የስራ እቅድ ነው፡፡ በነዚህ ዘጠኝ ተከታታይ ወራት ውስጥ አድዋን መሰረት በማድረግ ለአገራችን አንድነት መስዋእትነት የከፈሉ በተለያየ ዘመን የተነሱ ጀግኖችና የታሪክ ትሩፋታቸው እንደሚዘከሩ እንዲሁ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

    

 

 

ፀሐይቱ ሙዚቃዊ ቲያትር

 

 " በራፋቶኤል የማስታወቂያና ምዕላድ ድርጅት እየቀረበ የሚገኘው "ማዕደ አድዋ" የመታሰቢያ ትእይንት ሐምሌ 5 ቀን "ፀሐይቱ" የተሰኘ አጭር ሙዚቃዊ ቲያትር ለእይታ አብቅቷል። ይህ ሙዚቃዊ ቲያትር በእቴጌ ጣይቱ የህይወት ታሪክ ተመስርቶ የቀረበ ነበር። በእለቱ የክብር እንግዶች ስለእቴጌ ጣይቱ ጀግንነት ንግግር የተደረገ ሲሆን እንዲሁ ለአገራችን ነፃነት ከጥንት ጀምሮ አጥንታቸውን የከሰከሱ ደማቸውን ያፈሰሱ ሴት እናቶቻችንን ለማሰብ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል። 

ማእደ አድዋ 120ኛውን የአድዋ ድል በድምቀት ለተከታታይ ዘጠኝ ወራት ለማክበር የተዘጋጀ ትእይንት መሆኑን የድርጅቱ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ራፋቶኤል ወርቁ ገልፀዋል። "

      

119ኛው የአድዋ ድል በአል

ራፋቶኤል የማስታወቂያና ምዕላድ ድርጅት 119ኛውን የአድዋ ድል በአል የካቲት 23 ቀን 2007 ዓ.ም. በምኒሊክ ሀውልት ጉንጉን አበባ በማስቀመጥ ቀኑን ዘክሮ ውሏል፡፡ የአበባ ማስቀመጥ ስርአቱም የተካሄደው በታዳጊ ህጻናት እንደነበር ታውቋል፡፡ ይህም የሆነው ህጻናት የነገ አገር ተረካቢ በመሆናቸውና ያለፈ ታሪካቸውን የማወቅ ግዴታ ስላለባቸው መሆኑን የፕሮግራሙ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡