መፅሐፈ ፀሐይ

User Rating:  / 3

መፅሐፈ ፀሐይ

ሰአሉ ወይትወሀበክሙ ኅሱ ወትረክቡ ጎድጉዱ ወይትረኅወክሙ እስመ ኩሉ ዘይስእል ይንስእ ወዘሂ የኅስስ ይረክብ ወለዘሂ ጎድጎደ ይትረኅወ፡፡ ማቴ 7፡7  ለምኑ ይስጣችኋል ፈልጉ ታገኛላችሁ መዝጊያን አንኳኩ ይከፈትላችኃል የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና የሚፈልግም ያገኛል መዝጊያንም የሚያንኳኳ ይከፈትለታል ብሎ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረንን ትምህርት አብነት አድርገን  የኢትዮጵያ አገራችንን የቀደመ ምስጢራዊ ስልጣኔ ፍንጭ ለማግኘት የተለያዩ መዝጊያዎችን ማንኳኳት ከጀመርን ሰነባበትን፡፡ ታዲያ ቅዱስ ቃሉ እንደሚለውም ስለጥንቷ ኢትዮጵያ ምስጢራዊ ስልጣኔና ጥበባት ፍንጭ ለማግኘት ተነስተን አፍረን አናውቅም፡፡


በስነህዋ ምርምር ዙሪያ አገራችን ኢትዮጵያ ካሏት ጥንታዊ መፅሐፍት መካከል መፅሐፈ ራዚኤል(የሕይወት መፅሐፍ) መፅሐፈ ሔኖክ መፅሐፈ ብርሃን እና አቡሻህርን የመሳስሉት መፅሐፍት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ሲሆን ዛሬ የምናስተዋውቃችሁ መፅሐፍ ግን ከነዚህ መፅሐፍት በይዘቱ እጅግ የተለየ ምስጢራዊ የጥበብ መፅሐፍ ነው፡፡
ይህ መፅሐፍ መፅሐፈ ፀሐይ ይሰኛል፡፡ መፅሐፍ ፀሀይ መፅሐፈ ሔኖክ ከተፃፈበት ጊዜ አስቀድሞ እንደተፃፈ አንዳንድ ሊቃውንት አባቶች የሚያስተምሩ ሲሆን አጠቃላይ የፀሐይን የጨረቃን እንዲሁም የከዋክብትን ባህሪና እንቅስቃሴ እንዲሁም በሰው ልጆች ባህሪ ላይ ስለሚያሳድሩት ጠልሰማዊ ተፅእኖ በስፋት የተዘረዘረበት አስደናቂ መፅሐፍ ነው፡፡
ቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶች ዝናብ የማዝነብና የማቆም መንፈሳዊ ጥበባት የነበራቸው ሲሆን በዚህ በመፅሐፈ ፀሐይ ደግሞ የፀሐይን እንቅስቃሴና ብርሃኗን ይቆጣጠሩበት የነበረው አስደናቂ ጥበባት ተፅፈውበታል፡፡ አሁን በዚህ ፅሁፍ ከጠቀስነው አጭር የመፅሐፉ ይዘት በተጨማሪ በርካታ አስደናቂ ምስጢራዊ ጥበባትን እንደያዘ ምንጮቻችን አስረድተውናል፡፡
ጥንታዊ አባቶቻችን ከሰማያዊ ሃይላት ጋር ህብረት ፈጥረው ባገኙት ሰማያዊ ጥበብ ለአለሙ ማህበረሰብ የስልጣኔ ጮራን አንፀባርቃ እንደነበር ከምናቀርባቸው ማስረጃዎች እንድ ይህ መፅሐፈ ፀሐይ ነውና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ንቁ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲሁም ጥናትና ምርምር ሊያደርጉበት ይገባል መልእክታችን ነው፡፡ 

 

 

 

ይከተሉን!