ድርሳነ ማሕየዊ

ድርሳነ ማሕየዊ

ላለፉት ሰባት መቶ ዘመናት የዚች ቅድስት አገር ኢትዮጵያን ገናና ታሪክ ለማጥፋትና ምስጢራዊ ቅርሶቿን ለመዝረፍ ከላይ እታች ሲባጥጡ የነበሩት የምስጢር ማህበረሰቡ እርዝራዦች ያደረሱት ጥፋት ይህን ትውልድ ከአባቶቹ ጥበብ እንዲያፈነገጥ በር ከፍቶለታል፡፡ የስማዝያ ጭፍሮች በሆኑት የምስጢር ማህበረሰቡ ተላላኪዎች ተመዝብረው ተቃጥለው ተቆነፃፅለው በባሕር ተጥለው እንዲሁም ወደምእራቡ አለም ተሻግረው  በብዙ መቶ ሺህ  የሚቆጠሩ የጥበብና የምስጢር መፃሕፍትን አጥተናል፡፡ ቢሆንም ግን ምስጋና ለአያቶቻችን ይደረሳቸውን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ለዚህ ትውልድ የደረሱም በርካታ የጥበብ መፃሕፍት አሉ፡፡ በተጨማሪም አሁንም ድረስ ከስማዝያ ጭፍሮች ለመታደግ ሲባል በተለያዩ ዋሻዎች ውስጥ ተሰንቅረው የሚገኙእጅግ በርካታ መፅሐፍት እንዳሉ ከቅርብ ጊዜ አንስቶ በመገኘት ላይ የሚገኙ መይሐፍት ቃሚ ምስክር ናቸው፡፡ ታዲያ በአባቶቻችን ታላቅ መስዋእትነት ከዚህ ዘመን መድረስ ከቻሉት ጥንታዊ መፃፍት መካከል አንዱ ድርሳነ ማሕየዊ ነው፡፡

ድርሳነ ማሕየዊ ከማዋእለ ስብከቱ እስከ ዕለተ ሞቱ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካልተለዩትከቅዱሳት አንስት መካከል በኤልሳቤጥ በቤርዜዳንና በሜልቴዳን የተፃፈ ነው፡፡ ይህ መፅሐፍ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ተወልዶ በግዕዘ ሕፃናት አድጎ ከናዝሬት ወደገሊላ እየተመላለሰ ልዩ ልዩ ተአምራትን በማድረግና ምድርን በእግሩ እየቀደሳት  የወንጌልን መንግስት እያስተማረ የዚህን ዓለም ተልእኮውን አናውኖ ወደሰማይ ካረገ በኃላ ለሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸው ከፃፉት የወንጌል መፅሕፍት መካከል እንደ አንድ አካል ይቆጠራል፡፡ በዚህም ከአራቱ የወንጌል መፅሐፍት ባሻገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ስለጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስላስተማረው ትምህርትና በምድር ላይ በነበረው ቆይታ ስላደረጋቸው ተአምራትና ጠቅላላ ታሪክ ከማንም በተሻለ እንድትመሰክር ከሚያስችሏት በርካታ መፅሀፍት መካከል አንዱና ዋንኛው ነው፡፡
ድርሳነ ማኅየዊ ጌታችን በምድር ላይ የሰራውን ትሩፍት ያደረጋቸውን ተአምራት ለሰው ልጆች ሲል የተቀበለውን ለህሊና የሚከብድ ስቃይና መከራ በሰፊው የሚያትት ሲሆን ይህንኑ መፅሐፍ  እንዲሁ አያቶቻችን በፀሎቱ ኃይለቃል ድውይ ፈውሰውበታል የጎበጠ አቅንተውበታል እውር አብርተውበታል፡፡
ድርሳነ ማሕየዊን መሰል የቅዱሳት መፃሕፍት ቅርሶቻችን ለነገ ማንነታችን መሰረት ናቸውና ወጣቱ ትውልድ ነቅቶ ሊማራቸውና ሊያጠናቸው ይገባል፡፡ የድርጅታችን አላማም እነዚህን ጥንታዊ መፅሐፍት ማስተዋወቅ እንደመሆኑ ወደፊትም እንዲሁ ሌሎች የጥበብና የታሪክ መፃሕፍትን ለማስተዋወቅና ለመጠበቅ ጠንክረን እንደምንሰራ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

 

 

 

ይከተሉን!