ስለ ራፋቶኤል

ጥቂት ስለራፋቶኤል ምዕማር


       አገራችን ኢትዮጵያ አስራ ሶስት ወር ፀሃይ የሚፈራረቅባት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ ለኑሮ የሚመች የስልጣኔ የታሪክ የባህል የኪነጥበብ የሃይማኖት አሻራ ያረፈባት ቀደምትና ጥንታዊት ሀገር ናት፡፡ ጥንታውያን ኢትዮጵያውያን ለዘመኑ የዓለም ስልጣኔ መነሻ የሆኑ እና ለዘመኑ ምሁራን እንቆቅልሽ የሆኑ ጥበባዊ ስራዎችን አስረክበውን እነርሱ አልፈዋል፡፡ በእነርሱ ዘመን የማይሽረው መስዋእትነትም ለዓለማችን የታሪክ የባህል የስልጣኔ የፍልስፋና የነጻነት የአንድነት የጥበብና የምስጢራት ማእከልና መገኛ እንዲሁ ለዘመኑ ስልጣኔ ፈር ቀዳጅ መሆን ችላለች እናት አገራችን ኢትዮጵያ፡፡ ህያው ሆነው የሚኖሩት ቋሚ ቅርሶቻችንና የእነርሱ የስራ ውጤቶች የሆኑት ጥንታዊ መጻህፍቶቻችንም ይህንኑ ይተርኩልናል፡፡

Read more: ስለ ራፋቶኤል

ይከተሉን!